CG Amharic
Child Guidance Amharic
ይህ ሃና 4-14 ፖድካስት መንፈሳዊ የልጆች አስተዳደግን በተመለከተ Child Guidance ከተባለው መጽሐፍ ትምህርት የሚቀርብበት ነው። "ሃና 4-14" የሚለው ስያሜ ሃና ልጁዋን ሳሙኤልን ለእግዚአብሔር እንደሰጠች እኛም ልጆቻችንን ለእግዚአብሔር መንግስት ይበቁ ዘንድ በትክክለኛው መንገድ ኮትኩተን ለማሳደግ ጸሎታችን እንዲሆን በመመኘት የተሰጠ ሲሆን፣ እዲሁም "4-14" የሚለው ልጆቻችንን በዚህ እድሜ ክልል ውስጥ የሚያገኙት ምሪት ለህይወታቸው ትልቅ መሰረት የሚጥል መሆኑን ለማስታወስ ነው። ትምህርቱን በመከታተል እንድትባረኩበት ጸሎታች ነው።